10 በምሥራቅ አፍሪካ ግዙፍ ኩባንያዎች

0
881

ምንጭ፡-ምንጭ፤ አፍሪካን ቢዝነስ (2022)

ድህነትን በመታገልና ለውጥን ለማምጣት እየታገለች ያለችው አፍሪካ፣ ከብዙ ፈተናዎቿ ጎን ለጎን የሠራቻቸው የልማት ሥራዎችም አሉ። አፍሪካን ቢዝነስ በድረገጹ በጠቅላላው በአፍሪካ ቁንጮ ሆነው የታዩ ግዙፍ የሆኑ 250 ኩባንያዎችን ይዘረዝራል።

በዚህም ፈጠራን በማሳደግ፣ ስልታዊና ችግርን የሚቋቋም ንግድ ሥራ በመሥራት፣ ከፍተኛ ትርፍ በማግኘትና በመላው አፍሪካ በከፍተኛ መጠን ኢንቨስት በማድረግ ቀዳሚ የሆኑ ኩባንያዎች ሥማቸው ይጠቀሳል።

እኛም በዚህ በዐስርቱ ዝርዝር አኅጉሪቱን በተለያየ አቅጣጫ በማስተሳሰር የጎላ ድርሻ ባለው በምሥራቅ አፍሪካ የሚገኙትን ግዙፍ የተባሉ ኩባንያዎች በመለየት በዐስርቱ ዝርዝር ውስጥ አስቀምጠን ተመልክተናል። በዘህ መሠረት ኬንያ እና ታንዛኒያ እንዲሁም ሩዋንዳ እና ዩጋንዳ የአብዛኞቹ ግዙፍ ኩባንያዎች መገኛ ናቸው። በጠቅላላው በአፍሪካም ያለውን የምጣኔ ሀብት ደረጃ በማሳደግ ረገድ የእነዚህ አገራት ድርሻ የላቀ ነው። በጥቅሉ በአፍሪካ ደረጃ ሲታይ፣ በምሥራቅ አፍሪካ በአንደኛነት የሚገኘው ሳፋሪኮም 12ኛ ደረጃ ላይ ያለ ነው።


ቅጽ 4 ቁጥር 205 መስከረም 28 2015

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here