ማክሰኞ ኀዳር 6 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአባላቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ከሰጧቸው ምላሾች መካከል፦
👉 “የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ2014 የበጀት ዓመት መጨረሻ ላይ 6.16 ትሪሊየን ብር ደርሷል፡፡ በዶላር ሲሰላ 126.1 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል፡፡ የነፍስ ወከፍ ገቢ 1212 ዶላር ደርሷል፡፡”
👉 ከምሥራቅ አፍሪካ አንደኛው ግዙፉ ኢኮኖሚ፣ ከሰብ ሰሃራን አፍሪካ ኢኮኖሚ 3ኛው ጉዙፉ ኢኮኖሚ ሆኗል፤ ይሄ ዳታ የመንግሥታችን አይደለም፣ የወርልድ ባንክ ዳታ ነው” ብለዋል፡፡
👉“በዚህ ቁጥር ሙሉ በሙሉ አንስማማም፡፡ ምክንያቱም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ፎርማል ከሆነው ኢኮኖሚ ያልተናነሰ ኢንፎርማል አካውንት ለማድረግ የሚያስቸግሩ የኢኮኖሚ ትስስር አለው” ሲሉ ከቀረበው ቁጥር ሊልቅ እንደሚችል ገልጸዋል፡፡
👉የባለፈው ዓመት የአጠቃላይ የምርት መጠን (GDP) እድገት 6.4 በመቶ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ7.5 በመቶ ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል።
👉የዋጋ ንረት የዓለም ኹሉ ፈተና ነው፡፡ ያደጉና የበለጸጉ አገራትም በዋጋ ንረት ፈተና ውስጥ ገብተዋል፡፡
ምርቶች በጦርነት በግጭት ወደሚፈለገው ቀጠና እነዳይደርሱ በመደረጉ ነው፡፡
👉ባለፉት አራት ወራት የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት በመቀነስ ሒደት ላይ ነው፡፡
👉 የእሁድ ገበያ እየተለመደ መምጣቱ ገበያን ለማረጋጋት የራሱን ሚና እየተጫወተ ነው፡፡
👉 ኢትዮጵያ ዛሬ 9.5 ሚሊዮን ተማሪዎችን በቀን ኹለቴ ትመግባለች፤ ይሄ ሊጠናከር ይገባል፡፡
👉 በአዲስ አበባ ከተማ 30 ሺሕ ሰው በየ አካባቢው ሔዶ በነፃ የሚበላበት ሥፍራ አዘጋጅተናል፡፡
👉ኢትዮጵያ ውስጥ መሬት የመንግሥትም አይደለም፣ የሕዝብም አይደለም የደላሎች እና የሌቦች ሹመኞች ነው፡፡ ይሄ ሥር ነቀል ማስተካከያ ይፈልጋል፡፡ ሕገ መንግሥቱ የሕዝብና የመንግሥት ነው የሚለው ግን ደላሎች ወስደውታል፡፡ ይሄ የሚስተካከለው አካታች ብሔራዊ ውይይት ያልነውን በትክክል ስንነጋገር ነው፡፡
👉መሬት ቢያንስ የግለሰብ መሆን አለበት፡፡ ከፈለገ ባለቤቱ ይሽጠው፡፡ መንግሥት ወይ አይጠቀምበትም ወይ አይሸጠውም፡፡
👉 ከጥቅምት 4 ጀምሮ በውጭ ምንዛሪ ተገዝተው ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ የታገዱት 38 የሸቀጥ ዓይነቶች ላይ በዓመት አንድ ቢልየን ዶላር ወጪ ይደረጋል።
👉በአዲስ አበባ ከተማ ከ9 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች በቀን ኹለት ጊዜ እንዲመገቡ ማድረግ ተችሏል፡፡
👉ግዮን ሆቴልን ባለ ስድስት ኮከብ ሆቴል አድርጎ ለመገንባት ዝግጅት እየተደረገ ነው።



