ቢሮው የሲሚንቶ ምርት ላይ ከተተመነው ዋጋ በላይ በሚሸጡ አከፋፋዮች እና የችርቻሮ ድርጅቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ

0
878

ሐሙስ ሚያዚያ 26 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የሲሚንቶ ምርት ላይ ከተተመነው ዋጋ በላይ በሚሸጡ አከፋፋዮች እና የችርቻሮ ድርጅቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

ቢሮው በከተማዋ የሚታዩ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪዎችን ለመከላከል የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ የገለጸ ሲሆን፤ በዚህ መሰረት በሲሚንቶ ምርት ላይ ከተተመነው ዋጋ በላይ በሚሸጡ የንግድ ድርጅቶች ላይ ከማሸግ ጀምሮ ሌሎች ሕጋዊ እርምጃዎችን እንደሚወስድ አስታውቋል።

ሕብረተሰቡ በተለይም ሸማቾች ከተተመነው ዋጋ በላይ ከፍለው መሸመት የሌለባቸው ሲሆን፣ ጉዳዩ ሲያጋጥማቸው በነፃ የስልክ መስመር 8588 በመደወል ጥቆማ አድርሱኝ ሲልም ቢሮው ጠይቋል፡፡

በዚህም መሠረት፦
👉 ደርባ በ1 ሺሕ 67 ብር ከ36 ሳንቲም፣

👉 ዳንጎቴ 1 ሺሕ 106 ብር ከ85 ሳንቲም፣

👉 ሀበሻ በ1 ሺሕ 305 ብር፣

👉 ሙገር በ1 ሺሕ 16 ብር፣

👉 ኢትዮ 1 ሺሕ 56 ከ80 ሳንቲም፣

👉 ናሽናል 1 ሺሕ 169 ብር ከ98 ሳንቲም፣

👉 ካፒታል 1 ሺሕ 101 ብር ከ05 ሳንቲም የመሸጫ ዋጋ መሆኑን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here