ቦርዱ በሕወሓት ሥም ክልላዊ ፓርቲ ለመመሥረት የቀረበለትን የቅድመ ዕውቅና ጥያቄ ውድቅ አደረገ

0
749

ማክሰኞ ሰኔ 6 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት) ሥም ክልላዊ ፓርቲ ለመመሥረት የቀረበለትን የቅድመ ዕውቅና ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን አስታውቋል።

ቦርዱ በገብረ ሚካኤል ተስፋይ እና ሌሎች ሦስት ግለሰቦች አወያይነት ግንቦት 12/2015 በተደረገ ስብሰባ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ክልላዊ ፓርቲ ለመመስረት መወሰኑን የ120 መሰራች አባላት ዝርዝር በማያያዝ የቅድመ ዕውቅና ፈቃድ እንዲሰጠው ግንቦት 21/2015 በተፃፈ ደብዳቤ ጥያቄ እንደቀረበለት ገልጿል፡፡

ቦርዱ ግንቦት 25/2015 ባደረገው ስብሰባ የቀረበለትን የጊዜያዊ ፈቃድ ጥያቄ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች አንፃር መመርመሩን ገልጿል። በዚህም በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀፅ 86(1) እንደተገለጸው፤ ቦርዱ ይህን መሰል ጥያቄን በሚያስተናግድበት ወቅት የምዝገባ ጥያቄ ቀረበበት ስያሜ ወይም አህፅሮተ ሥም በምርጫም ጊዜም ሆነ ከምርጫ ውጪ በዜጎች ዘንድ መምታታትን ወይም ግርታን የማይፈጥር መሆኑን ሊያረጋግጥ እንደሚገባው አመላክቷል።

በሌላ በኩል “ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)” በሚል ስያሜ እየተጠራ በትግራይ ክልልም ይሁን በሌሎች የአገራችን ክፍሎች በሚገኙ መራጮች ዘንድ ለረጅም ዓመታት የሚታወቅ ፓርቲ የነበረ በመሆኑ፤ ግለሰቦቹ አዲስ ፓርቲ ቢያቋቁሙ መራጮችን ያደናግራል በማለት የፈቃድ ጥያቄውን አለመቀበሉን ቦርዱ አስታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here