እስራኤል የኢትዮጵያ መንግሥት የዴር ሡልጣን ገዳም ይዞታን እንዲያስጠብቅ አሳሰበች

0
641

ረቡዕ ሰኔ 28 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ)

በግብፅ ኮፕቲክና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  መካከል አለመግባባት የሚፈጥረው የዴር ሡልጣን ገዳም ይዞታ፤ የኢትዮጵያ ሆኖ እንዲዘልቅ እንደሚፈልግ የእስራኤል መንግሥት ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ኢየሩሳሌም የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ንብረት የሆነውን የዴር ሡልጣን ገዳም ይዞታ ማስጠበቅ አለበት ሲሉ፤ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

 

የእስራኤል መንግሥት የዴር ሡልጣን ገዳም የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተክርስቲያን  ይዞታ  ነው ብሎ እንደሚያምንም አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡

ነገር ግን ጉዳዩ የፖለቲካ ጥቅም ግጭት ያለበት በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመሆን ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት እንዳለበት ነው ያስታወቁት።     

ከአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በገዳምነት ይጠቀሙበትና ይኖሩበት እንደነበር የሚነገርለት በእስራኤል ጎለጎታ ተራራ ላይ የሚገኘው የዴር ሡልጣን ገዳም፤ በተለያየ ጊዜ የባለቤትነት ጥያቄ ይነሳበታል፡፡          

በተለይ የግብፅ ኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን የባለቤትነት ጥያቄ ስታነሳ ቆይታለች፡፡ በተደጋጋሚም ገዳሙ ውዝግብና ግጭቶችን ያስተናግዳል፡፡

ይዞታዉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተክርስቲያን  እንደሆነ ቢነገርም፤ ግብጻውያኑም የይገባኛል ጥያቄ በማንሳት ለዘመናት ዉጥረትን የሚያስተናግድ ቦታ ነዉ፡፡   

አምባሳደር አለልኝ ቀደም ባለዉ ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን አባቶች በገዳሙ ዉስጥ እንዲጠለሉ አንድ የግብጽ መነኩሴ በማስጠጋታቸዉ ግብጾቹ የእኛነዉ የሚል እሳቤ እንዳደረባቸዉና ከዚያ በኋላ የይገባኛል ጥያቄ ማንሳት መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡

በዴር-ሡልጣን ገዳም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን፣ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን፣ የሮማን ካቶሊካዉያን ቤተክርስቲያን፣ የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን፣ የአርመን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና የግብጽ ኮፕት ቤተክርስቲያን እንደሚገኙበት ይነገራል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here