ከ24 ሚሊዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ከጅቡቲ ወደብ ወደ አገር ውስጥ እየተጓጓዘ እንደሚገኝ ተገለጸ

0
311

ረቡዕ ነሐሴ 10 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) መንግሥት የኑሮ ወድነትን ለማሻሻልና ገበያ ለማረጋጋት ተከታታይነት ያለው እርምጃ እወስዳለው ባለው መሠረት 24 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ከጅቡቲ ወደ የተለያዩ የአገራችን ክፍሎች እየተጓጓዘ እንደሚገኝ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

የምግብ ዘይቱ በኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አማካኝነት በኹለት ምዕራፍ ወደ አገር የሚገባ ሲሆን፤ ይህ የፍጆታ ዕቃ በዋናኝነት የኑሮ ውድነትን ለማሻሻልና ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት ታስቦ በመንግሥት የተደረገ ግዢ ነው ተብሏል።በማጓጓዝ ሥራው የጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፓርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ከኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ጋር በመቀናጀት በተቀላጠፈ መልኩ እየተሰራ እንደሚገኝም ተገልጿል።

በዚህም መሰረት በመጀመሪያ የኦፕሬሽን ምዕራፍ 11 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ወደ አገር ውስጥ መላክ መቻሉ የተገለጸ ሲሆን፤ በኹለተኛ ምዕራፍም 13 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ አገር ቤት እንዲገባ በመሰራት ላይ እንደሚገኝ ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here