የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

0
445

አርብ ነሐሴ 12 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የተባበሩት አረብ ኢሜሬቶች ፕሬዚዳንት ሼክ ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ “ውድ ወንድሜ እና ጓደኛዬ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጣህ” ብለዋል፡፡

እያደገ የመጣው የኹለቱ ሀገራት ግንኙነት በመከባበር እና ለጋራ እድገት የጋራ ራዕይ ላይ የተመሰረተ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “ዘላቂ ልማትን ለማስቀጠል ትብብራችንን እንቀጥላለንም” ብለዋል።የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ በኢትዮጵያ ቆይታቸውም ከተለያዩ የመንግሥት የሥራ ኃፊዎች ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡

ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ከሆኑ በኋላ በኢትዮጵያ ጉብኝት ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያቸው ነው፡፡ ከዚህ ቀደም የቡዳቢ አልጋ ወራሽ በነበሩትበት ወቅት በ2018 በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገው እንደነበር ይታወሳል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here