ሐሙስ መስከረም 24 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የኢፌዴሪ አየር ኃይል አካዳሚ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ላለፉት ስድስት ወራት መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና ሲከታተሉ የነበሩ ምልምል ወታደሮችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡
በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳን ጨምሮ ሌሎች የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በመርኃ ግብሩ በ1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ዓመት በበረራና ቴክኒሻን የሙያ ዘርፎች ትምህርትና ሥልጠናቸውን እየተከታተሉ ለሚገኙ ሠልጣኞች የትከሻ ምልክት (ፍላግ) የማልበስ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።



