በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በመሰጠት ላይ ነው

0
241

ማክሰኞ መስከረም 29 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በትግራይ ክልል በ2012 የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኝ የነበሩና መልቀቂያ ፈተናውን ሳይወሰዱ ለቀሩ ተማሪዎች የሚሰጠው የመልቀቂያ ፈተና በዛሬው ዕለት መሰጠት ጀምሯል፡፡

በዚህም መሰረት በክልሉ 9 ሺሕ 514 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የመልቀቂያ ፈተና እንደሚወስዱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ከዚህም ውስጥ 6 ሺሕ 513 ተማሪዎች የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ሲሆኑ፤ 3 ሺሕ 1 የሚሆኑት ደግሞ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች መሆናቸውን ቢሮው ገልጿል፡፡

ፈተናው ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ሲሆን፤ ተማሪዎቹ በመቀሌ፣ በአክሱም፣ በአዲግራት እና በራያ ዩኒቨርሲቲዎች ፈተናውን በመውሰድ ላይ ይገኛሉ፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here