በኢትዮጵያና በቻይና መካከል በተለያዩ መስኮች አስራ ኹለት የትብብር ስምምነቶች ተፈረሙ

0
204

ሰኞ ጥቅምት 5 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ቻይና ቤጂንግ ያቀኑ ሲሆን፤ ቻይና ሲደርሱም በአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ይፋዊ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።ከአቀባበል ሥነ ስርዓቱ በኋላም ጠቅላይ ሚኒስትሮቹ የኹለትዮሽ ውይይት ያካሄዱ ሲሆን፤ በዚህም በኹለቱ አገራት መካከል ያለውን የምጣኔ ኃብት ትብብር ግንኙነት ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ከኹለትዮሽ ውይይቱ በመቀጠልም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ጠቅላይ ሚ ሊ ኪያንግ በተገኙበት በኹለቱ አገራት መካከል በተለያዩ መስኮች 12 ያህል የትብብር ስምምነቶች እና ኹለት የፍላጎት ሰነዶች ተፈርመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቻይና ይፋዊ ጉብኝት ሲያደርጉ ከአራት ዓመት በኃላ ይህ የመጀመሪያቸው ሲሆን፤ በቀጣይ በሚካሄደው 3ኛው የቤልት ኤንድ ሮድ አለም አቀፍ ትብብር መድረክ ላይም ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here