ፕሮፌሰር ጌትነት ታደለ የ2023 የብሔራዊ አመራር ሽልማት ተሸላሚ ሆኑ

0
205

ሰኞ ጥቅምት 5 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁር የሆኑት ፕሮፌሰር ጌትነት ታደለ፤ አውስትራሊያ ከሚገኘው የኒውካስል ዩኒቨርሲቲ “የ2023 አሉምናይ ልህቀት ሽልማት” በብሔራዊ አመራርነት ዘርፍ አሸናፊ ሆነዋል።

ሽልማቱ ፕሮፌሰር ጌትነት በማህበረሰብ ለውጥ ላደረጉት በጎ አስተዋፅኦ የተሰጠ ዕውቅና መሆኑን ዩንቨርስቲው ገልጿል።

የኒውካስል ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪው ፕሮፌሰር ጌትነት በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሶሾዮሎጂ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ሲሆኑ፤ ለረጅም ዓመታት በሶሲዮሎጂ እና ጤና መካከል ያለውን ዝምድና ሲመራመሩ፣ ሲያስተምሩ እና የጥናት ውጤቶቻቸውን በታዋቂ አለም አቀፍ መጽሄቶች በማሳተም ግኝቶቻቸውን ለሌሎች ሲያካፍሉ የኖሩ ኢትዮጵያዊ ምሁር ናቸው፡፡ከ45 በላይ በጥናት እና ምርምር የተሰሩ ጽሑፎችን እና የመጽሐፍት ምዕራፎችን በታወቁ አለም አቀፍ መጽሔቶችና መጽሐፍት ላይ ያሳተሙ ሲሆን፤ ሦስት መጽሐፍትን ራሳቸው እና ከባልደረቦቻቸው ጋር ሆነው ጽፈው በማሳተም ለተደራሲያን አቅርበዋል፡፡

በተጨማሪም በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ትምህርት ቤቶችን በማስገንባት ለማኅበረሰቡ አበርክተዋል፡፡

ፕሮፌሰር ጌትነት በማህበራዊ ጥናት ዘርፍ የ2013 የበጎ ሰው ሽልማት ተሸላሚ እንደነበሩም ይታወሳል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here