ኤርትራ የባህር በር ጉዳይ ላይ ለድርድር እንደማትቀመጥ አስታወቀች

0
245

ሰኞ ጥቅምት 5 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተነሳዉ የባህር በር ጉዳይ ላይ፤ ኤርትራ ለድርድር እንደማትቀመጥ የኤርትራ መንግሥት የመረጃ ሚኒስትር አስታውቋል፡፡

የኤርትራ መንግሥት የመረጃ ሚኒስትር ዛሬ ባወጣው አጭር መግለጫ፤ “በቅርብ ጊዜ ስለ ውሃ እና ስለ ባህር በሮች እንዲሁም ተመሳሳይ ርዕሰ ጉዳዮች የተነገረው እና የተባለው ቁጥር የለውም” ያለ ሲሆን፤ “በዚም ያልተገረመ ታዛቢ የለም” ብሏል፡፡

የኤርትራ መንግሥትም እንደኹልጊዜው በእንደዚህ ዓይነቱ ጉዳዮች ላይ ለውይይት እንደማይታደም ያስታወቀው ሚኒስቴሩ፤ ይህ ነገር ይመለከተናል የሚሉ ኹሉም አካላት ጉዳዩን እንዳይነኩት በመግለጫው ማሳሰቡን አዲስ ማለዳ ከሚኒስቴሩ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አርብ ጥቅምት 2/2016 ምሽት፤ በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በተላለፈውና ‹‹ከጠብታ ውኃ እስከ ባሕር ውኃ›› የሚል ርዕስ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ባደረጉት ገለጻ፤ ቀይ ባህርን አስመልክተው ማብራሪያ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡

በመግለጫቸውም፤ “በታሪክ፣ በጂኦግራፊ፣ በዘር (በብሄር) እና በኦኮኖሚ ምክንያቶች የቀይ ባህር ጉዳይ ይመለከተናል።” ያሉ ሲሆን፤ “ቀይ ባህር ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ እንጂ ቅብጠት አይደለም። አባይና ቀይ ባህር የኢትዮጵያን ልማትና ጥፋት የሚወስኑ የኢትዮጵያ የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ናቸው።” ብለዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here