የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነት ወደ ኹኔታ የማይፈታው ስልታዊ ትብብር እና ወዳጅነት ደረጃ ከፍ ማለቱ ተገለጸ

0
140

ማክሰኞ ጥቅምት 6 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ ከየልዑካን ቡድናቸው ጋር በመሆን በቻይና ታላቁ የሕዝብ አዳራሽ የኹለትዮሽ ውይይት አድርገዋል፡፡

በኹለትዮሽ ውይይቱ ወቅት ፕሬዝዳንት ሺ በኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀል ኹነት ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንኳን ደስ ያለዎት ብለዋቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነትም ከኹሉን አቀፍ ፅኑ ግንኙነት፤ ወደ ኹኔታ የማይፈታው ስልታዊ ትብብር እና ወዳጅነት ደረጃ ከፍ ማለቱን በይፋ አብስረዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አድንቀው ከቻይናው አረንጓዴ ልማት ፖሊሲ ጋር ተናባቢ በመሆኑ የግሪን ቤልት እና ሮድ አካል ሆኖ ሊደገፍ እንደሚችል ማረጋገጣቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቻይና ኢንቨስትመንት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እመርታ የሚኖረውን አስተዋፅዖት አንስተዋል። በተለይም በአምስቱ ቁልፍ ምሰሶዎች-በግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ አይሲቲ፣ ማእድን ልማት እና ቱሪዝም ተጨማሪ ኢንቨስትመንት እንዲኖር የማበረታቻ ጥሪ ማቅረባቸውን ጽሕፈት ቤቱ ገልጿል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here