ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ የቤት ለቤት የፓስፖርት አገልግሎት መሰጠት እንደሚጀምር ተገለጸ

0
596

ዓርብ ሐምሌ 05ቀን 2016(አዲስ ማለዳ) የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የቤት ለቤት የፓስፖርት አገልግሎት እንደሚጀምር አስታውቋል።

የቤት ለቤት አገልግሎት የሚሰጠው ለየት ባለ እና ተጨማሪ ክፍያን በሚጠይቅ መልኩ ሲሆን አገልግሎቱ በልዩ ሁኔታና ደረጃ እንደሚሰጥ ተጠቁሟል፡፡

አገልግሎቱ የ 2016 አመት የስራ አፈጻጸሙን በማስመልከት በሰጠው መግለጫ በበጀት ዓመቱ በርካታ ማሻሻያ መደረጋቸው ያነሳ ሲሆን 14.7 ቢሊዮን ብር ገቢ እንዳገኘም አስታውቋል፡፡

ይህ አገልግሎት በባለሃብቶች እና ታዋቂ ሰዎች ጥያቄ መሰረት ለመጀመር መታቀዱን የገለጸው ተቋሙ አዲሱ የፓስፖርት እደላ አገልግሎት የተለየ ክፍያ የሚተመንለት ስለመሆኑ ነው የጠቆመው፡፡

የፓስፖርት አገልግሎቱን ለማሳመን አዳዲስ አሰራሮችን ይፋ እንደሚያደርግ በመግለጽም አሁን ላይ ፓስፖርት የማሰራጨት አቅሙን በቀን ከ2ሺህ ወደ 14 ሺህ ማሳደጉን አንስቷል፡፡

ይሁን እንጂ ተቋሙ ይህን ቢልም ፓስፖርት ለማግኘት ወራትን መጠበቅ ግድ የሆነባቸው ተገልጋዮች በተቋሙ አሰራር በተደጋጋሚ ሲማረሩ ይደመጣሉ፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here