የፌደራል እና የክልል መንግስታት በግዛት ክልላቸው የሚፈጸመውን ኢሰብአዊ ደርጊት ለማስቆም በሚፈለገው ደረጃ ተግባራዊ እንቅስቃሴ አላደረጉም ተባለ

0
480

የፌደራል እና የክልል መንግስታት በግዛት ክልላቸው የሚፈጸመውን ግድያ፣ እገታ እና አስገድዶ መሰወር ለማስቆም በሚፈለገው ደረጃ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ባለማድረጋቸው ይህ ድርጊት በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋና እየተባባሰ ነው ሲል ኢሰመጉ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ባወጣው መግለጫ የሰዎች በሕይወት የመኖር መብት፣ የአካል ደህንነት መብት እና ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብት አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰ መሆኑን በመረጃ በማስደገፍ በተደጋጋሚ መግለጫዎችን ያወጣ ቢሆንም የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን እርምጃ አለመውሰዳቸው ማህበረሰቡን ለከፍተኛ ምሬት እና እንግልት እየዳረገው ነው ብሏል፡፡

ኢሰመጉ አሰባስቢያለሁ ባለው መረጃም በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ግድያን ጨምሮ አፈናና ከህግ ውጪ የሚፈጸሙ የዘፈቀደ እስሮች ተባብሰው ቀጥለዋል ነው ያለው፡፡

ከኦሮሚያ ክልል ውጪ ባሉ በሌሎች ክልሎችም ተመሳሳይ ድርጊቶች የዘውትር ተግባራት ሆነዋል ያለው ጉባኤው የመንግስት የመጀመሪያ ሃላፊነት የሆነው የዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ ጉዳይም ተዳክሟል ብሏል በመግለጫው፡፡

በመሆኑም ኢሰመጉ የፌደራል መንግስት ሁሉንም የሰላም አማራጭ በሆደ ሰፊነት ተመልክቶ ነገሮችን ያስተካክል ሲል ምክረሃሳቡን አስቀምጧል፡፡

በተጨማሪም መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት፣ የሚድያ አካላት፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ሰብዓዊ መብት ላይ የሚሰሩ የሲቪል ማህበራት እንዲሁም በሰላም ግንባታ ላይ የሚሰሩ አካላት በአገር ውስጥ የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ፣ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እንዲሁም ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የበኩላቸውን አሰተዋጽኦ ተወጥተዋል ተብሎ እንደማይታሰብም ገልጿል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here