በጎፋ ዞን ባጋጠመ የመሬት ናዳ ከ20 በላይ ሰዎች ህይወት አለፈ

0
618

ሐምሌ 15 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበል ዛሬ ሰኞ ከረፋዱ 4:00 ሰዓት አካባቢ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ የበርካታ ሰዎች ሕይወት አልፏል።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ምስክር ምትኩ አደጋውን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፥  እሰካሁን በተደረገው ፍለጋ ከ 20 በላይ አስከሬን መገኘቱንና የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ጠቁመዋል።

በስፍራው ለነፍስ አድን የተሰበሰቡ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ  የአካባቢው ነዋሪዎችም የአደጋው ሰለባ መሆናቸውን አቶ ምስክር ተናግረዋል።

በአደጋው ሰለባ ከሆኑት ሰዎች መካከል የወረዳው ፖሊስ አባላትን ጨምሮ ሴቶችና ሕፃናት እንደሚገኙበት ተገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት የአስክሬን ፍለጋና የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ዋና አስተዳዳሪው አስረድተዋል።

የዞኑ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ማርቆስ መለሰ በበኩላቸው በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችን በመለየት የነፍስ አድን ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ስለመግለጻቸው አዲስ ማለዳ ከጎፋ ዞን መንግስት ኮምንኬሽን ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here