ሐምሌ 16 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ እስካሁን የሟቾች ቀጥር ከ146 በላይ መድረሱ ተገለፀ።
የዞኑ የመንግስት ረዳት ተጠሪና የፖለቲካና ሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ እና አስቸኳይ የአደጋ ጊዜ መልሶ ማቋቋሚያ ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሀብታሙ ፌተና አደጋውን አስመልክተው የሰጡትን መግለጫ አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።
በመግለጫቸውም እስካሁን በተደረገው ፍለጋ ሴቶችና ሕፃናትን ጨምሮ ወንድ 96 እና ሴት 50 በድምሩ የ146 ሰዎች አስክሬን የተገኘ ሲሆን፣ የአስክሬን ፍለጋ አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።
የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችልና የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን አቶ ሀብታሙ ተናግረዋል።



