በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የ243 ሰዎች አስክሬን ተገኝቶ በክብር እንዲያርፍ የተደረገ ሲሆን የ6 ሰዎች እስክሬን ግን አልተገኘም ተብሏል

0
425

ዕረቡ ሐምሌ 24 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የቀሪ ሰዎችን አስክሬን የማፈላለጉ ሥራ ማብቃቱን ዛሬ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት አሳውቋል።

ያልተገኙ ሟቾችን የመፈለጉ ሥራ ያበቃው አደጋው ከተከሰተበት ከባለፈው ሐምሌ 15 ቀን ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ የቁፋሮ ሥራው ሲካሄድ ከቆየ በኋላ እንደሆነ ጠቁሟል።

በፍለጋው የ243 ሰዎች አስክሬን በማግኘት በክብር እንዲያርፍ ሲደረግ፤ የ6 ሰዎች እስክሬን ግን እስከ ትናንት ተፈልጎ አለመገኘቱን አሳውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here