የፌደራል መንግሥት 551 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርብ ተገለጸ

ሰኞ ሐምሌ 29ቀም2016(አዲስ ማለዳ)የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ የፌደራል መንግሥት 551 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርብ ተናግረዋል፡፡

በበጀት መልክ ለፓርላማ ከሚቀርበው ግማሽ ትሪሊዮን ብር ውስጥ 240 ቢሊዮን የሚሆነው ለማኅበራዊ ድጋፍ፣ለሴፍቲኔት፣ለሠራተኛ ደመወዝ ጭማሪ፣ ለመድኃኒት ድጎማ፣ ለዘይት ድጎማ፣ ለነዳጅ ድጎማ የሚውል መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

በመሆኑም 563 ቢሊዮን የነበረው የፌደራል መንግሥት ገቢ ተከልሶ 851 ቢሊዮን ይሆናል፤ ይህም የፌደራል መንግስት ዓመታዊ በጀትም ለመጀመሪያ ጊዜ ከ1 ትሪሊዮን እንዲሻገር ያደርገዋል።

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ከአንድ ወር በፊት አንድ ትሪሊዮን ብር የሚጠጋ በጀት ማጽደቁ ያታወሳል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here