በወላይታ ዞን በደረሰ የመሬት ናዳ የ11 ሰዎች ህይወት አለፈ

ሰኞ ሐምሌ 29ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ ዛሬ ረፋድ 5 ሠዓት አካባቢ በተከሰተ የመሬት ናዳ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

በተከሰተው አደጋ እስካሁን በተደረገ ፍለጋ የ11 አስከሬን የተገኘ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል የካዎ ኮይሻ ወረዳ አስተዳደር አሳውቋል።

ከቀናት በፊት በዚሁ አካባቢ በተከሰተ የመሬት ናዳ 1 ሰው ህይወቱ ማለፉ እና 1 ሰው ከባድ ጉዳት እንደረሰበት ይታወሳል።
በደቡብና ደቡብ ምእራብ ኢትዮጲያ የተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመው የመሬት ናዳ አደጋ የበርካቶች ህይወት ያለፈ ሲሆን በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ነዋሪዎችም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here