አቶ ኡሞድ ኡጅሉ ከስልጣን ተነሱ

0
497

ማክሰኞ ነሐሴ 07 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) አቶ ኡሞድ ኡጅሉ ከስልጣን መነሳታቸውን አዲስ ማለዳ በክልሉ ከሚገኙ ምንጮቿ አሰምታለች።

ፕሬዝዳንት ኡሞድ ኡጅሉ ከስልጣን መነሳታቸውን ተከትሎ በርካታ የከተማዋ ወጣቶች ደሰታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው ተብሏል።

በአንጻሩ የኡሞድ ኡጁሉ ደጋፊወች ፕሬዚደንቱ ለምን ከስልጣን ተነሱ ብለው የንግድ መደብሮችን እና ሱቆችን ዝጉ፣ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች እና ሞተር ሳይክሎች እንዳይንቀሳቀሱ፣ለማድረግ ፡በራሪ ወረቀት ሲበተኑ መመልከታቸውን አዲስ ማለዳ ከምንጮቿ አሰምታለች።

ይህን ተከትሎም በፕሬዚዳንቱ ከስልጣን መነሳት ቅር የተሰኙት እና በፕሬዚዳንቱ ተቃዋሚዎች መካከል የፀጥታ ችግር እንዳይከሰት በሚል መከላከያና የፌደራል ፖሊስ በከተማው በብዛት በመንቀሳቀስ ላይ ስለመሆናቸው ተሰምቷል።

የክልሉ ፕሬዲንቱ ኡመድ ኡጁሉ ከስልጣን መነሳታቸውን ተከትሎ አለሚቱ ኦመድ በጊዚያዊነት የክልሉ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሰሩ የፌደራሉ መንግሥት ስለመመደቡ አዲስ ማለዳ ከምንጮቿ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here