ማክሰኞ 07 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ድርጅቱ ህጋዊ እውቅና እንዳያገኝና ጉባኤ እንዳያካሂድ የሚያደናቅፍ ከፍተኛ አመራር በድርጅቱ ውስጥ ተፈጥሩኣል ሲሉ የህወሀት ሊቀመንበሩ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ሊቀመንበሩ የዚህ ጉባዔ ዋና ዓላማ ድርጅቱን አድኖ ህዝብን ከጥፋት ማዳን ነው ተብለዋል።
የህወሃት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ድርጅታችንና ህዝባችን የሚድኑት በዚህ ጉባዔ ነው ሲሊ መግጻቸውን አዲስ ማለዳ ከምንጮቿ አሰምታለች።
ሊቀመንበሩ አክለውም ሙሉ በሙሉ እንድንድን በዴሞክራሲያዊ መንገድ ክርክርና ውይይት ሙሉ ብቃት ያላቸው አመራር ሊመረጡ ይገባል ሲሉ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ደብረፅዮን(ዶ/ር) ይሄ ጉባኤ የድርጅቱም የህዝቡም የሞት ሽረት ጉዳይ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።



