ረቡዕ ነሐሴ 8 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ ነገ እንደሚካሄድ የክልሉ ምክር ቤት አስታውቋል።
ለአንድ ቀን በሚካሄደው ጉባኤ ምክር ቤቱ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት በማድረግ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍም ይጠበቃል።
የክልሉ ፕሬዲንቱ ኡመድ ኡጁሉ ከስልጣን መነሳታቸውን ተከትሎ ወ/ሮ አለሚቱ ኦመድ በጊዚያዊነት የክልሉ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲሰሩ ስለመመደባቸው አዲስ ማለዳ መዘገቧ ይታወሳል።



