እያደረኩኝ ባለሁት ሰላምን የማፈላለግ ሂደት ስሜ አላግባብ እየጠፋ ነው ሲል የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል አስታወቀ

ረቡዕ ነሐሴ 8 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በአማራ ክልል እየተደረገ ያለውን ጦርነት ለማስቆም እና መንግስትና በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ሃሎችን ወደ ድርድር እንዲቀርቡ ሁኔታዎችን የሚያመቻች የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል የተባለ አደረጃጀት ከወራ በፊት በክልሉ መዲና ባህርዳር መቋቋሙ ይታወሳል፡፡

ሰላም በክልሉ እንዲመጣና ህዝቡ ወደ ቀደመ እንቅስቃሴው እንዲመለስ የሚያስችል ስራ እየሰራ ስለመሆኑ ደጋግሞ የሚገልጸው የሰላም ካውንስሉ ሰላምን ለማምጣት እያከናወንኳቸው ባሉ ጥረቶች ላይ ግን የስም ማጥፋት ዘመቻዎች እየተከፈቱብኝ ነው ብሏል፡፡

በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ሃይሎች አንስቶ እስከ ክልሉ ባለስልጣናት ድረስ ጦርነት ስለሚቆምበት ሁኔታ በተደጋጋሚ ንግግር ስለማድረጉ የሚገልጸው ካውንስሉ በተለያዩ አካላት እየተነሳብኝ ያለው የስም ማጥፋት ዘመቻ ግን በምፈልገው ልክ እንድሄድ እያደረገኝ አይደለም ሲል ይገልጻል፡፡

ከአዲስ ማለዳ ጋር ቆይታ ያደረጉት የሰላም ካውንስሉ ሰብሳቢ አቶ ያየህ ይራድ በለጠ የሰላም ካውንስሉ እየሄደበት ያለው መንገድ ብዙ ፖለቲካዊ የቤት ስራዎችን የሚጠይቅ መሆኑን ከግምት ሊገባ ይገባል ብለዋል፡፡

ያባልሆነበት እና ነባራዊ ሁኔታዎችን ከግምት አስገብቶ ባልታየበት ሁኔታ የሚሰጡ አስተያየቶችም ተገቢነት የሌላቸው ናቸው ብለዋል ዋና ሰብሳቢው፡፡

ከታማኒነት፤ከገለልተኝነትና ከመሰል ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ጥያቄዎች በተደጋጋሚ የሚነሱበት የሰላም ካውንስሉ ከየትኛው የፋኖ አደረጃጀት አመራርም ይሁን ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተው ስለማውራታቸው ግን በግልጽ ያስቀመጡት ነገር እንደሌለ የሚታወቅ ነው፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here