በህወሓት ጉባኤ “የሚተላለፉ ውሳኔዎች ተቀባይነት የላቸውም” ሲል በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ቡድን አስታወቀ

0
289

ሰኞ ነሐሴ 13 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በደብረጺዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት 14ኛ ፓርቲ ጉባኤ ዛሬ ከሰአት እንደሚጠናቀቅ ያሳወቀ ሲሆን በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት ስብሰባ ተጠናቆ መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫውም በህወሓት ጉባኤ “የሚተላለፉ ውሳኔዎች ተቀባይነት የላቸውም” ብሏል።

በመቀሌ ሰማእታት ሐወልት አደራሽ በመካሄድ ላይ ባለው የህወሓት ጉባኤ “የሚተላለፉ ውሳኔዎች ተቀባይነት የላቸውም” ሲል በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ቡድን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የተጠራ “ህወሓትን የማዳን” በሚል በመቀሌ ትላንት እሁድ ነሃሴ 12 ቀን 2016 ዓ.ም የተካሄደው ስብሰባ ተጠናቋል፤ በስብሰባው መጠናቀቂያ ላይ ተሰብሳቢዎቹ ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።

በዚህም “በህገወጡ ጉባኤ ሳቢያ ለሚመጡ አደጋዎች ሁሉ ተጠያቂው ይህ ቡድን ሀላፊነቱን ይወስዳል” ሲል አስጠንቅቋል።

በሌላ በኩል ጉባኤ በማካሄድ ላይ ያለው በሊቀመንበሩ ደብረጺዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ቡድን በበኩሉ ላለፉት 7 ቀናት ሲያካሂደው የነበረውን ጉባኤውን ዛሬ ነሃሴ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰአት በኋላ እነደሚያጠናቅቅ አስታውቋል።

በደብረጺዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ቡድን ዛሬ ከሰአት በኋላ በሚያጠናቅቀው ጉባኤ አዳዲስ ውሳኔዎችን ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ ጉባኤ ላይ “የሚተላለፉ ውሳኔዎች ተቀባይነት የላቸውም” ሲል በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ቡድን ውሳኔውን ከወዲሁ አጣጥሎታል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here