ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌ ብር ሱፐር አፕ ቪዛ ካርድን መጠቀም የሚያስችል አገልግሎት አስጀመረ

0
289

👉🏿አገልግሎቱ ሀገር ውስጥ የሚላከውን የገንዘብ መጠን (ሬሜታንስ) እንደሚያሳድ ታምኖበታል

ሰኞ ነሐሴ 13 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌ ብር ሱፐር አፕ አማካኝነት ቪዛ ካርድን መጠቀም የሚያስችል አገልግሎት ይፋ አድርጓል።

አገልግሎቱን ኢትዮ ቴሌኮም፣ ቪዛ ካርድ እና አቢሲኒያ ባንክ በዛሬው ዕለት በጋራ አስጀምረውታል፡፡

ቪዛ ዳይሬክትና ቴሌብር ሬሚት አፕን በቴሌብር ሱፐር አፕ በማውረድ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ፣ አገልገሎቱ ዜጎች በየትኛውም ሀገር ሆነው የእጅ ስልካቸውን በመጠቀም ገንዘብ የሚልኩበትና የሚቀበሉበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አገልግሎቱ በ190 ሀገራት የሚኖሩ ዜጎች የቪዛ ዳይሬክትን ተጠቅመው በቀላሉ ብር መላክ እና መቀበል የሚችሉበት መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም ለአዲስ ማለዳ በላከው ጋዜጣዊ መግለጫ ተመላክቷል፡፡

 

ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌ ብር ሱፐር አፕ ቪዛ ካርድን መጠቀም የሚያስችል አገልግሎት ማስጀመር መቻሉ ወደ ሀገር ውስጥ የሚላከውን የገንዘብ መጠን ያሳድጋል ተብሎ ከወዲሁ ታምኖበታል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here