በኢትዮጵያ ለ4 ክልል ያህል የቀረበ ህዝብ በአገር ውስጥ መፈናቀሉን አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አስታወቀ

0
223

ሰኞ ነሐሴ 13 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በኢትዮጵያ 3.3 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በአገር ውስጥ መፈናቀላቸውን ገልጿል፡፡

ይህ አሃዝ በአገሪቱ ካለው የ4 ክልሎች ህዝብ ጋር የሚጠጋጋ እንደሆነም ይገመታል፡፡

ግጭት፤ ከፍተኛ የዝናብ መጠን እንዲሁም በቂ የምግብ ዋስትና አለመኖር ለመፈናቀሉ ዋነኛ ምክንያት መሆናቸውን የጠቀሰው የድርጅቱ ሪፖርት በአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ የተፈናቃይ ቁጥር ካለባቸው አገራት ውስጥ ከሱዳንና ሱማሊያ በመቀጠል ኢትዮጵያ አንዷ እንደሆነችም አንስቷል።

በሰሜኑ ጦርነት እንዲሁም ኦሮሚያን ጨምሮ በሌሎች ክልሎች እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶች በርካቶች ከቤት ንብረታቸው እንዲፈናቀሉ ገፊ ምክንያቶች እንደሆኑ ተደጋግሞ ይነሳል፡፡

የድርጅቱ ሪፖርት እንዳመላከተውም በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት 20.1 ሚሊዮን የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መኖራቸውን ገልጾ፣ ይህ ቁጥር በሰኔ ወር ከነበረበት 19.2 ሚሊዮን በሐምሌ ወር ወደ 20.1 ሚሊዮን ማሻቀቡን ነው የጠቆመው፡፡

በሌላ በኩል ከፍተኛ የውጭ አገራት ስደተኞችን በመቀበል ኢትዮጲያ ከኡጋንዳ በመቀጠል ሁለተኛዋ አገር ስትሆን 1 ሚሊየን የውጭ አገር ስደተኞችን እንደተቀበለችም ድርጅቱ ያወጣው ሪፖርት ያመላክታል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here