አቶ ጌታቸዉ ረዳ ከሃላፊነታቸው ተነሱ

0
642

👉🏿 ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ዳግመኛ የህወሓት ሊቀመንበር ሆነዉ ተመርጠዋል

ሰኞ ነሐሴ 13 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) አቶ ጌታቸዉ ረዳ ከምክትልነት ቦታቸዉ ተነስተዉ አቶ አማኑኤል ተስፋይ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።

ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ሆነው በድጋሚ መመረጣቸውን ፓርቲው አሳውቋል።

አቶ አማኑኤል አሰፋ አቶ ጌታቸው ረዳን በመተካት የፓርቲው የምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።

ህወሓት ሁለቱን የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮች ምርጫ ያደረገው ላለፉት ስድስት ቀናት በመቀለ ከተማ ሲያደርገው የነበረውን አወዛጋቢ ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ባጠናቀቀበት ወቅት ነው።

በዛሬው የጉባኤ ውሎ፤ ዘጠኝ አባላት ያሉበት የህወሓት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫም መደረጉን አዲስ ማለዳ ከምንጮቿ ሰምታለች።

ይሁን እንጂ በህወሓት ጉባኤ “የሚተላለፉ ውሳኔዎች ተቀባይነት የላቸውም” ሲል በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የህወሓት ቡድን ማስታወቁን አዲስ ማለዳ መዘገቧ አይዘነጋም፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here