ሰኞ ነሐሴ 13 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) አዲሱ ስርዓተ ትምህርት አንድ ተማሪ 3 ቋንቋዎችን እንዲናገር የሚያስችል መሆኑን በሚኒስቴሩ የተፈጥሮ ሳይንስ ስርዓተ ትምህርት ዝግጅት ኃላፊ ዛፏ አብርሃ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ገልፀዋል።
ተማሪዎች በቅድመ አንደኛ ደረጃ በአፍ መፍቻ ቋንቋ፣ በአንደኛ ደረጃ ዓለም አቀፍ ቋንቋ ማለትም እንግሊዝኛ ከዚያም ከ3ኛ ክፍል በኋላ ሌላ የአጎራባች ክልል ቋንቋ እንደሚማሩ ኃላፊዋ አስረድተዋል።
የአጎራባች ክልል ቋንቋውም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሳይሆን በክልሎች የሚመረጥ እንደሆነም ነው የገለፁት።
በሥርዓተ ትምህርቱ ችግሮች ዙሪያ ከመምህራን፣ ከወላጆች እና ከተማሪዎች የሚነሱ ሀሳቦችንም እንመለከታለን ነው ያሉት ኃላፊዋ።
የመጽሐፍ ስርጭትን በተመለከተም ያሉ የበጀት ችግሮችን በመቋቋም በአማካይ ያለውን ተደራሽነት ለመጨመር እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።
በዚህም 18 ሚሊዮን መጻሕፍት ጅቡቲ መድረሳቸውን ጠቁመዋል።



