የአሸንድዬ፣ ሻደይ፣ አሸንዳ እና ሶለል በዓል በዛሬው እለት እየተከበረ ነው 

0
245

ሐሙስ ነሐሴ 16 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በኢትዮጵያ የሰሜኑ ክፍል በዋናነት በአማራ እና ትግራይ ክልሎች በደማቅ የልጃገረዶች ጭፈራ እና ዝማሬ ይከበራል፤ በዓሉ ከፍልሰታ ፆም ማብቃት ጋር ተያይዞ ከነሃሴ 16 ጀምሮ ይከወናል።

በሴቶች ዝማሬ የሚዋበው ይህ ባህላዊ ጭፈራ እና በዓል በየዕድሜ ደረጃው ያሉና በቡድን የሚሰበሰቡ ሕጻናት፣ ልጃገረዶችና እናቶች ቢሆኑም የጨዋታው ባለቤቶች በዋናነት ልጃገረዶች ወይም ያላገቡ እንስቶች ናቸው።

በዚህ ወር በትግራይ አሸንዳ፣ በዋግኽምራ ሻደይ፣ በራያ ሶለል፣ በላሊበላ አሸንድዬ፣ በሰሜን፣ ደቡብ እና ማዕከላዊ ጎንደር አሸንዴ (አሸንድዬ)፣ በምስራቅ ጎጃም አሸንድዬ ወይም እንግጫ ነቀላ ተብለው የሚጠሩ ድንቅ የልጃገረዶች ክብረ በዓላት አሉ።

በዓላቱ የአዲስ ዘመንን መምጣት፣ የሜዳው መለምለም እና ማበብ ምክንያት በማድረግ በሕጻናት፣ ልጃገረዶችና ወጣቶች የሚከበሩ የደስታና የነፃነት በዓላት ናቸው።

ህጻናትና ወጣት ሴቶች የአሸንድዬዉን ቅጠል ቆርጠዉ በወገባቸዉ በማሸረጥ እና አደይ አበባ በመያዝ ይጫወታሉ ፤ ይኸዉም ቀልብን የሚገዛ ድንቅ መንፈሳዊ ሀብት እና የባህል ዕሴት እንዲሆን አስችሎታል።

‘አሸንዳ’ ማለት በትግርኛ ርጥብ ገሣ (ሣር) ማለት ሲሆን፤ ነጭ ሽንኩርት ቅጠል የሚመስል ሰፊ እና ረዥም ተክል ነው፡፡

ዳገታማ ከሆኑ ቦታዎች እንደሚገኝ የሚነገርለት ይህ ተክል አሸንዳ ተብሎ ለሚታወቀው የበዓሉ ስያሜ መነሻ ነው።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here