በቃሊቲ የከፍተኛ ማረሚያ ቤት የሚገኙ የሞት ፍርደኞች ውሳኔው እንዲፈጸምባቸው ፕሬዝዳንቷን ተማጸኑ

0
518

ሐሙስ ነሐሴ 16 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙና የሞት ፍርድ የተወሰነባቸው ታራሚዎች ቅጣቱ እንዲፈጸም የሀገሪቱን ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴን የጠየቁበትን ደብዳቤ አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።

አስከፊ በሚባል የሰብአዊ መብት አያያዝና አለም አቀፍ የታራሚዎች አያያዘን በጣሰ መልኩ ላለፉት 17 ዓመታት በእስር ላይ እንገኛለን ያሉት ታራሚዎቹ የእርምት ሁኔታና የእስር ቆይታ ታይቶ ከማህበረሰቡ ጋር እንድንቀላቀል የተደነገገውን ህግ ተነፍገናል ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

የሞት ፍርዱ እንዲፈጸምባቸው የጠየቁት በለጠ አሰፋ ፣ ጀቤሳ ድንቁ ፣ ባዩ ጌታነህ ፣ ግርማ ገዛኸኝ እና መስታወት ጌታነህ የተባሉ ታራሚዎች ናቸው።

ታራሚዎቹ ፤ አሁን ላይ የኢትዮጵያ ፍትሕ ሚኒስቴር በሚሰጠው ምህረትና ይቅርታ ተጠቃሚ አለመሆናቸውንና ነገ የሚሉት ተስፋ እንደሌላቸው በመግለጽ ፕሬዝዳንቷ በቶሎ ጥያቄአችንን እንዲቀበሉን ሲሉም ጠይቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሞት ፍርድ በርዕሰ-ብሄሩ እስካልጸደቀ ድረስ ተፈጻሚነት እንደሌለው የአገሪቱ ህገ-መንግስት በግልጽ ይደነግጋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here