የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች መረጃ እንዳይሰጡ  በበላይ ሃላፊዎች ጫና እንደሚደርስባቸው ገለጹ

0
414

ቅዳሜ ነሐሴ 18 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የመንግስት ተቋማት ላይ የሚሰሩ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች መረጃ እንዳይሰጡ በበላይ ሃላፊዎች ጫና እንደሚደርስባቸው ገለጸዋል።

ይህ የተባለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የመረጃ ነጻነት እና የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ 590/2000 ለማሻሻያ የቀረበ ረቂቅ ሰነድ ዙሪያ

ከፌደራል እና አዲስ አበባ ከተማ መስሪያ ቤቶች የህዝብ ግንኙነት ሀላፊዎች፣ የመንግስትና የግል የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት እና የሲቪክ ማህበራት ጋር ባደረገው የግብአት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ነው።

የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎቹ የተቋማቸውን የስራ አፈጻጸም ፣ቀጣይ እቅድና መሰል መድረኮች ላይ ተሳታፊ የማይሆኑበት ሁኔታ እንዳለ በመኖሩ ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን መረጃ በሚጠየቁበት ወቅት ለጉዳዩ እንግዳ እንደሚሆኑ ይናገራሉ።

ከዚህ ባለፈም የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎቹ የሚያውቁትን መረጃ  ጭምር ለመገናኛ ብዙሃን እንዳይናገሩ በበላይ ሃላፊዎች ጫና እንደሚደርስባቸው ነው የጠቆሙት ።

ከ2010 ዓ.ም በፊት የነበረው የመረጃ አሰጣጥ ሂደት በቀደመው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር  በኩል የሚያልፍና ተቋማትን ተጠያቂ የሚያደርግ ነበር ያሉት ባለሙያዎቹ አሁን ላይ ያለው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ግን የመረጃ አሰጣጥ ሂደትን በመከታተል ረገድ ስራ ውጤታማ ስራ እየሰራ ነው ለማለት እንደሚቸግራቸው ይገልጻሉ።

በተለይም የተዛቡ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች በሚሰራጩበት ወቅት እንኳን የመረጃውን ሀሰተኛነት የሚገልጽ አካል እንደሌለና በቸልተኝነት የሚታለፉ ስለመሆኑ ባለሙያዎቹ አብራርተዋል።

በመሆኑም መረጃ አልሰጣችሁም ተብለን ልንወቀስ አይገባም ያሉት እነዚህ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች አሁንላይ ያለው የመረጃ አሰጣጥ ፍሰት የተፋለሰ፣ ወጥ የሆነ የአሰራር ስርአት የሌለው እና አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰ መሆኑን አንስተዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here