በሰሜን ጎንደር በመሬት መንሸራተት የ10 ሰዎች ሕይወት አለፈ

0
271

ቅዳሜ ነሐሴ 18 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ አብና ቀበሌ ልዩ ስሙ ኖላ በተባለ ቦታ በመሬት መንሸራተት አደጋ የ10 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ስምንት ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደረሰባቸዋል፡፡

የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች በደጃች ሜዳ ጤና ጣቢያ የሕክምና እርዳታ እያገኙ መሆኑን የወረዳው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተስፋዬ ወርቅነህ ተናግረዋል፡፡

በአደጋው ምክንያት 480 አባወራዎች እና 2 ሺህ 400 የቤተሰብ አባላት  መፈናቀላቸውን በመጥቀስ በጊዜያዊ መጠለያዎች እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

ከ35 በላይ የቤት እንሰሳት መሞታቸውን እና ከ30 ሔክታር በላይ በሰብል የተሸፈነ መሬትም ከጥቅም ውጭ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here