ኤርቪን ማሲንጋ በእነ ደብረጺዮን ህወሓት እና በጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራሮች መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ መቀሌ ገቡ

0
433

ሰኞ ነሐሴ 20 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በደብረጺዮን ገብረሚካኤል(ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት እና በጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚደንት አቶ ጌታቸው ቡድን መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ መቀሌ ገብተዋል።

ማሲንጋ መቀሌ ሲደርሱ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ እና ምክትል ፕሬዜዳንቱ ጄነራል ታደሰ ወረደ ተቀብለዋቸዋል።

በቆይታቸው በወቅታዊ የትግራይ የፖለቲካ ሁኔታ፣ በተፈናቃዮች መመለስ ጉዳይ እና ሁለቱ የህወሓት አመራር ቡድኖች መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ ከእነ ደብረጺዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) እና ከጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here