👉🏿ተጠርጣሪዎቹ በጠበቆቻቸው በኩል የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።
ሰኞ ነሐሴ 20 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት የፌዴራል ፖሊስ በእነ ዮሐንስ ዳንኤል ላይ በጠየቀው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ላይ የግራ ቀኙን ሰፊ ክርክር ካዳመጠ በኋላ ብይን ለመስጠት ለነገ ነሐሴ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።
የፌዴሬል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን ተጠርጣሪዎቹ ላይ የአቪዬሽን አሰራር ሕግ ከመጣስ ባለፈ በሽብር ወንጀልም ምርመራ ስለጀመርኩ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ ይደረግ በማለት ተከራክሯል።
ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎች ዮሐንስ ዳንኤል ፣ አማኑኤል መውጫ ፣ ናትናኤል ወንድወሰን ፣ ኤልያስ ድሪባ ፣ ይዲድያ ነጻነት እና እሌኒ ክንፈ ተክለአብ ናቸው።
የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ መዝገብ እንደሚያሳየው እነዚህ ተጠርጣሪዎች ተፈጥሮ በፈጠረው የአየር መዛባት ምክንያት አውሮፕላኑ መብረር አይችልም እየተባለ፣ አስገድዶ ለማስኬድ የፈጠሩት አምባጓሮ በወንጀል ሕጉ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል ብሏል።
ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባር መጠቀም ሲገባቸው፣ የሀገር ኩራት እና የራሳቸው ንብረት የሆነውን አየር መንገድ ማንቋሸሻቸው አሳዛኝ ተግባር ስለመሆኑ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ መግለፁን አዲስ ማለዳ በትናንት ጥንቅሯ መዘገቧ ይታወሳል።



