ረቡዕ ነሐሴ 2 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በኦሮሚያ ክልል ተፈርዶባቸው እስር ላይ የነበሩ 3 ሺህ 611 ታራሚዎች በይቅርታ ከእስር እንዲፈቱ መወሰኑን የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አሳውቋል።
በክልሉ በይቅርታ ከእስር እንዲፈቱ ከተወሰነላቸው አጠቃላይ እስረኞች መካከል 2 መቶ 47ቱ ሴቶች መሆናቸው ተጠቁሟል።
ከእስረኞቹ መካከል የሞት ቅጣት ያለባቸው የህግ ታራሚዎች፤ ተደጋጋሚ ወንጀል የፈጸሙ እና ሀሰተኛ ማስረጃ በማዘጋጀትና በማሰራጨት የተጠየቁ የህግ ታራሚዎችን ይቅርታው አያካትትም ተብሏል።
የይቅርታው መስፈርትም በማረሚያ ቤት ቆይታቸው የታረሙ ፤ ከተጎጂ ቤተሰብ ጋር የታረቁ ፤ የገንዘብ መቀጮ የከፈሉና ይቅርታ እንዲደረግላቸው የጠየቁ ናቸው ሲል የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጠቁሟል።



