አምባሳደ ሌንጮ ባቲ በአሜሪካ መንግስት ተቀባይነት አጡ 

0
634

ሐሙስ ነሐሴ 23 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ከጥቂት ሳምንታት በፊት ወደ አዲስ አበባ የተጠሩትን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ኢ/ር ስለሺ በቀለን እንዲተኩ የተመረጡት አምባሳደር ሌንጮ ባቲ በአሜሪካ መንግስት ተቀባይነት ማጣታቸውን ምንጮች ጠቁመውናል።

እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉትን አምባሳደር ሌንጮን አሜሪካ እንደማትቀበል ገልፃ እሳቸውን የሚተካ ስው እንዲላክላት ጠይቃለች ተብሏል።

ምክንያቱ ምን ይሆን ለሚው ጉዳዩን የሚያውቁ ምንጮች አምባሳደር ሌንጮ ከአመታት በፊት በአሜሪካን ሀገር ሲኖሩ ከነበረባቸው አንዳንድ ክሶች ጋር የተያያዘ እንደሆነ ጠቁመው ዝርዝር ጉዳዩን ማንሳት ግን እንደማይፈልጉ ከመሠረት ሚዲያ ተሰምቷል።

“እነዚህ ክሶች በህዝብ ማህደር (public record) ውስጥ ስላሉ አሜሪካኖቹ አምባሳደሩ በሀገራቸው እንዲሾሙ አልፈለጉም። ይህንን ጉዳይ አሜሪካኖቹ ለኢትዮጵያ መንግስት አሳውቀዋል” ብለው ምንጮቹ ተናግረዋል።

በጉዳዩ ዙርያ እስካሁን በኢትዮጵያ መንግስት የተሰጠ ማረጋገጫም ይሁን ማብራርያ የለም።

አሜሪካ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች በሀገሯ ሲሾሙ የራሷን መስፈርት በማስቀመጥ የምትመረምር ሲሆን በበርካታ አጋጣሚዎች የሌላ ሀገራት አምባሳደሮችን ሳትቀበል ቀርታለች።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here