<< የደሴ ህዝብ እየተረሳ ነው›› የከተማ አስተዳደሩ

👉🏿የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገልን ነው ለማለት አንደፍርም

አርብ ነሐሴ 24 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ከሳምንት በፊት በደሴ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ አሁንም መቀጠሉን የደሴ ከተማ አስተዳር አስታውቋል፡፡

ቤቶች እየፈረሱ፣ተፈናቃይ ዜጎችም ቁጥራቸው እያሻቀበ ነው ያሉት በደሴ ከተማ የአራዳ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ግርማ ይህ ነው የሚባል ትኩረትም ለአደጋው አለመሰጠቱት ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጲያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲቲዩት የመሬት መንሸራተት አደጋ ስጋ አለባቸው ብሎ ከለያቸው አካባቢዎች ደሴ ከተማ አንዷ ብትሆንም ይህ ነው የሚባል የቅድመ -መከላከል እንቅስቃሴዎች እየተከናወኑ አይደለም ሲሉ ቅሬታቸውን ለአዲስ ማለዳ ገልቷል፡፡

የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ለአንድ ጊዜ ብቻ 15 ኪሎ ዱቀቄት ከመስጠቱ ባለፈ የችግሩን ጥልቃጥ ገምግሞ ተከታታይ ድጋፍ አላደረገልንም ያሉት ሃላፊው በየቀኑ የተፈናቃዮች ቁጥርም አሳሳቢ በሚባል ደረጃ እየጨመረ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

አሁን ላይም በከተማዋ ከ375 በላይ ዜጎች ተፈናቅለውበአስቸጋ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ገልጸው ይህ የወንዶችን ቁጥር የሚያካትት እንዳልሆነም አንስተዋል፡፡

አሁን ላይ የተፈናቀሉ ዜጎችም በትምህርት ቤቶች ውስጥ በጊዚያዊነት ተጠልለው እነደሚገኙ የገለጹት ሃላፊው መጪው የትምህርት ዘመን ከመቃረቡ ጋር ተያይዞ ነዋሪዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም ሁሉም ዜጋ ለከተማዋ ድጋፍ እንዲያደርግ ተማጽነዋል፡፡

በአደጋው ዙሪያ አዲስ ማዳ የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ሃላፊዎችን ለማናገር ያደረገችው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here