“ሱማሊያ በቀጣናው ያልተገባ እንቅስቃሴ እያደረገች ነው” ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ 

0
304

እሁድ ጳጉሜ 03 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ጎረቤት አገር ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ጋር በመሆን በቀጠናው ያልተገባ እንቅስቃሴ እያደረገች ነው ሲሉ ወቀሱ።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ቅዳሜ ጵጉሜ 02/2016 ዓ.ም. በምስራቅ ዕዝ 47ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓል የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር “የኢትዮጵያ መልማት የሚያንገበግባት ታሪካዊ ጠላታችን ከሩቅ መጥታ ለሶማሊያውያን ወዳጅ መስላ ታሪካዊ ዓላማውን ለማሳካት” እየተንቀሳቃሰች ነው ብለዋል።

ምንም እንኳ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በዚህ ንግግራቸው የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ያሏትን ሀገር በስም ባይጠቅሱም፤ ይህን ንግግራቸው የተሰማው በቅርቡ ሶማሊያ እና ግብጽ የደረሱትን ወታደራዊ ስምምነት ተከትሎ ካይሮ ጦሯን ሞቃዲሾ አስገብታ በቀጠናው ውጥረት ካየለ በኋላ ነው።

የግብጽ ጦር አውሮፕላኖች ሶማሊያ መድረሳቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያ ባወጣችው መግለጫ የግብጽ ጦር በሶማሊያ እንዲሰማራ መደረጉ ለሶማሊያ እና ለአጠቃላዩ የአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት እና ደኅንነት አሳሳቢ ነው ማለቷ አይዘነጋም ።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here