ቅዳሜ ጳጉሜ 2 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት ዛሬ በአክሱም ሊካሄድ የታቀደው ህዝባዊ ውይይት መሰረዙን ከጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ዛሬ የወጣው መረጃ ይጠቁማል።
የጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤቱ ፕሬዜዳንቱ ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት ከአክሱም ከተማና አከባቢዋ ነዋሪዎች ጋር ሊካሄድ እቅድ የተያዘለት ህዝባዊ ውይይት ሳይካሄድ በመቅረቱ ይቅርታ ጠይቋል።
ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ያጋጠማቸው የጤና እክል ቀላል ይሁን ከባድ በመግለጫው የተባለ ነገር የለም።
ከሰሞኑን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ምክትላቸው ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ያሉበት የአመራሮች ቡድን በየከተማው ህዝባዊ ምክክር እያደረገ እንደነበር አዲስ ማለዳ መዘገቧ አይዘነጋም።



