ሰኞ ጳጉሜ 04 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቅርብም በሩቅም ያሉ አካላት እኛ ኢትዮጵያዊያን ነን ፤ የሰው አንፈልግም፤ የሚፈልገንና የሚነካንን ግን እንደ ልማዳችን አሳፍረን እንመልሳለን ሲሉ አሳስበዋል፡፡
የትኛውም አገር “ኢትዮጵያን መድፈር ሲፈልግ አንዴ ሳይሆን አስር ጊዜ ማሰብ ይኖርበታል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኛ በኩል ምንም አይነት የጦርነትና የግጭት ፍላጎት የለም” ሲሉም ተደምጠዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢትዮጵያ ከአንዳንድ አገራት ጋር ግጭት ልትገባ እንደምትችል የሚነገሩ ንግግሮች አሉ” ሲሉ የተደመጡት ጠ/ሚኒስትሩ እሳቸው በሥልጣን ላይ የቆዩባቸውን ያለፉትን ስድስት አመታት ተኩል በመጥቀስ “በአንድም ጎረቤት ላይ አንድም ጥይት ተኩሰን አናውቅም” ብለዋል።
ወደ ውጪ የምንሄደው፤ ወንድሞቻችን ሲቸግራቸው፤ ሰላም እና የእኛን የሙያ ድጋፍ ሲፈልጉ ብቻ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
በቅርብም በሩቅም ያሉ አካላት እኛ ኢትዮጵያዊያን ነን፤ የሰው አንፈልግም፤ የሚፈልገንና የሚነካንን ግን እንደ ልማዳችን አሳፍረን እንመልሳለን ሲሉም አሳስበዋል።



