የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ምንም አይነት አስተዳደራዊ ሹምሽር እንዳይሰጥ ታገደ

0
440

ማክሰኞ ጳጉሜ 05 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዚያዊ አስተዳደር አዲስ ሹመት ስጠትም ሆነ መሻር  እንዳችል መታገዱን የትግራይ ጸጥታ ሃይሎች ሃላፊ ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ አስታውቋል፡፡

ይህ እንዲሆን የተወሰነው በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር እና በደብረፂዮን ገ/ሚካኤል በሚመራው የህወሓት ቡድን መካከል የተፈጠረው ልዩነት እየሰፋ በመሄዱ እንደሆነ የገለጹት ጄነራል ታደሰ ይህ ውሳኔ ይህንን ልዩነት ለማጥበብ ታስቦ የተወሰነ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

በህወሃት ውስጥ የተከሰተው መከፋፈል ተከትሎ የተከሰተው ውጥረት አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡

በአቶ ጌታቸው ረዳና በዶክተር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል ቡድን መካከል የተፈጠረው ክፍፍል ዋነኛ ምክንያቱ ስልጣን ነው የሚሉ ተቺዎች ሁለቱም ቡድኖች በድህረ-ጦርነት ውስጥ የሚገኘውን የክልሉን ህዝብ ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መንገድ ስራ እየሰሩ አይደለም ሲሉ ወቀሳ ሲያቀርቡባቸው ይደመጣል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here