‹‹ተፈናቃዮችን ከትምህርት ቤቶች የማስወጣት ስራ እየተሰራ ነው›› የደሴ ከተማ አስተዳደር

0
408

አርብ መስከረም 03 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በአማራ ክልል ደሴ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ የማቋቋም ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በደሴ ከተማ የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ግርማ እንዳስታወቁት መጪው ጊዜ የትምህርት ወቅት እንደመሆኑና ተፈናቃዮችን በቋሚነት እንዲሰፍሩ ለማድረግ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በአደጋው ንብረታቸው የወደመ እና ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች አሁንም በጊዜያዊ ማቆያ ካምፖች ውስጥ የሚገኙ ቢሆንም በወደሙ ንብረቶች ላይ የተለያዩ ጥናቶች ተደርገው ለመልሶ ማልማት ወደ ክልሉ ከተማ አስተዳደር እንደተላከ ስራ አስፈጻሚው ጠቁመዋል፡፡

አክለውም የክረምቱ የዝናብ መጠን መቀነሱን ተከትሎ የአደጋ ስጋቱ አንጻራዊ የመሻሻል ሁኔታ አያሳየ መሆኑን እንዲሁም አስፈላጊው እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ሃላፊው ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ቤቶች እየፈረሱ፣ተፈናቃይ ዜጎችም ቁጥራቸው እያሻቀበ ነው ይህ ነው የሚባል ትኩረትም ለአደጋው አልተሰጠም እንዲሁም  የቅድመ መከላከል እንቅስቃሴዎች እየተከናወኑ አይደለም ማለታቸው አይዘነጋም፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here