የድምፃዊ ንዋይ ደበበ እና የአይዳ ሐሰን ወንድ ልጅ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

0
811

ቅዳሜ መስከረም 04 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በትዳር ሕይወታቸው ፅናት ነዋይ የተባለች ሴት ልጅና ሰላም ነዋይ የተባለ ወንድ ልጅ በጋራ ያፈሩት ንዋይና አይዳ ልጆቻቸውን ያሳደጉት ቨርጂንያ ውስጥ ሲሆን፣ ሰላም ከጊዜ በኋላ በገጠመው የጤና እክል የተነሳ ሕክምና ሲከታተል ቆይቷል።

በተለይ የኩላሊት ኢንፌክሽን ተጠቂ በነበረበት ሰዓት አንድ ኩላሊት እናቱ አይዳ ሰጥታው ንቅለ ተከላ ማድረጉ ይታወሳል።

ከልጅነቱ ጀምሮ ተጨዋች፣ ሳቂታ እና ቀልድ የሚወድ ተወዳጅ ልጅ እንደነበር የተመሰከረለት ሰላም ነዋይ ትምህርቱን ተከታትሎ ያጠናቀቀው እዚያው አሜሪካን አገር ሲሆን፣ ሲበዛ አዛኝ ልብ የነበረውና ሰዎችን መርዳት የሚያስደስተው ሰላም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

አዲስ ማለዳ ለነዋይ ደበበና መላው ቤተሰቡ መጽናናትን ትመኛለች።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here