”ብልፅግና ፓርቲ የሕዝብን ሀብት እየመዘበረ ነው ”- ኢዜማ

ሰኞ መሰከረም 06 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) በአዳማ ከተማ እየተካሄዳ ላለው የብልፅግና ፓርቲ አባላት ሥልጠና ከመንግሥት ካዝና ገንዘብ ወጥቶ መከፈሉ የህዝብ ሃብት እየተመዘበረ ስለመሆኑ ማሳያ ነው ሲል በመግለጫው ተችቷል፡፡

የፌደራል ዋና ኦዲተር እና የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ይሄንን ጉዳይ ተከታትለው ከሕግ አግባብ ውጪ የሕዝብ ሀብትን የዘረፈውን የመንግሥት አካል ተጠያቂ እንዲያደርጉ እና ጉዳዩን በይፋ ለሕዝብ እንዲያሳውቁ ጠይቃለው የሚለው ፓርቲው ይሁን እንጂ አጥጋቢ ምላሽ አለማግኘቱን አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ”እንደ ባለፈው ዓመት ሁሉ ዘንድሮም ብልጽግና ፓርቲ በተመሳሳይ መንገድ ያንኑ ስህተት በአደባባይ እየደገመው ነው ብሏል፡፡

ይህም አካሄድ ገዢው ፓርቲ የመንግሥት እና የፓርቲ ሥራ መለያየት አለበት የሚለውን የፖለቲካ እውቀት ካለመረዳት የሚሠራው ስህተት ሳይሆን የማናለብኝነት መንገድን መርጦ በእብሪተኝነት እየተጓዘ ስለመሆኑ ማሳያ ነው ብሏል፡፡

አሁን ላይም ለአባላቱ እየከፈለ ያለው የውሎ አበልና ተያያዥ ወጪዎች ከድሃ መቀነት የተፈታና ከድሃው ህዝብ የተሰበሰበ መሆኑን አውቆ ከእንደዚህ አይነት ኢ-ዲሞክራሲያዊና የአገር ሃብት በዝባዥ ከሆነ አካሄድ ሊቆጠብ ይገባል ብሏል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here