እሁድ መስከረም 05 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በዓሉ የሐይማኖት አባቶች፣ የእምነቱ ተከታዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ከማለዳው ጀምሮ በተለያዩ ሐይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች በመከበር ላይ ነው።
በአንዋር መስጂድ እየተከበረ ያለውን በዓል የታላቁ አንዋር መስጂድ ኢማም ሸህ ጣኻ ሀሩን ቁርአን በመቅራትና ዱዓ በማድረግ በይፋ የሚያስጀምሩት ይሆናል።
በዓሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ በታላቁ አንዋር መስጂድ በሰደቃ፣ በመንዙማና በነሺዳ በሀይማኖት አባቶች እና በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በመከበር ላይ ይገኛል።



