ማክሰኞ መስከረም 07 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) “ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በኢትዮዽያ ገንቢ የፖለቲካ ባህል ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ምልክት ነበሩ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፡፡
ረዘም ላለ ጊዜ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ስሰማ ከልብ አዝኛለሁ ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
” ያቆዩት ውርስ እና ቅርስ ፀንቶ እንዲቀጥል ነፍሳቸውም በሰላም እንድታርፍ እመኛለሁ።” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሐዘን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡



