ከ1 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ለበጀት አመቱ እቅድ ማስፈፀሚያ ተመድቧል- ኢትዮ ቴሌኮም

ሐሙስ መስከረም 09 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ኢትዮ ቴሌኮም በ2017 አዲስ በጀት አመት የማሻሻያ እና የግንባታ እቅዶችን ወደ ተግባር ለመቀየር ከ1ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ በጀት መመደቡን አስታውቋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንደገለፁት በዚህ አመት የደንበኞችን ቁጥር ወደ 83 ሚሊዮን ከማሳደግ ታቅዷል ብለዋል።

አክለውም በባለፈው አመት አጠቃላይ ገቢ ከ93ቢሊየን ብር በላይ የተገኘ ሲሆን በ2017 መጨረሻ 163 ቢሊየን ብር ገቢ ለማድረስ እንደሚሰራ አመላክተዋል።

በቴሌ ብር አገልግሎት ላለፋት 3 አመታት 3.7 ትሪሊየን ብር መዘዋወሩን ያስታወሱ ሲሆን በአሁኑ አመትም በተሻለ መንገድ ለማዘመን እና ተጠቃሚዎችን ወደ 15 ሚሊዮን ለማስፋት መታቀዱን ጠቁመዋል።

የተደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ታሳቢ ያደረገ እቅድ የወጣ መሆኑን እና ለውጪ ኢንቨስተሮች በጋራ ለመስራት እድል እንደሚከፍትም ተመላክቷል ።

እንዲሁም በተለያዩ የገጠር ከተሞች ተደራሽነት በማስፋት ለ1ሺ ቀበሌ ነዋሪዎች ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል አገልግሎት እንደሚዘረጋ ተገልጿል።

በተጨማሪ የ130አመት የስራ ዘመን ቆይታን በማስመልከት ለ6ወር የሚቆይ ኢትዮ 130 የተባለ የተለያዩ ሽልማቶችን የያዘ የሞባይል ጨዋታ አስተዋውቀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here