ጊዜያዊ አስተዳደሩ አስተዳደራዊ ስራዎችን መምራት እንጂ የትግራይ ሰራዊትን ማዘዝ አይችልም ሲሉ ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ገለጹ

0
426

ረቡዕ መስከረም 14 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በደብረጺዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት በመስከረም 14 መግለጫው “ጊዜያዊ አስተዳደሩ ስሙ እንደሚያመለክተው አስተዳደራዊ ስራዎችን እያከናወነ በአጭር ግዜ እንደመሸጋገሪያ የሚያገለግል እንጂ የትግራይ ሰራዊትን በስሩ አድርጎ በዕዝ ሰንሰለት ለመምራት የተሰጠው ተልእኮ፣ መዋቅርም ሆነ አደረጃጀት የለውም” ሲል ገልጿል።

በተጨማሪም አሁን ባለው አደረጃጀት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ተጠሪነቱ ለፌደራል መንግስቱ መሆኑን ያመላከተው መግለጫው የትግራይ ሰራዊት በጊዜያዊ አስተዳደሩ ስር እንዲሆን ማድረግ ማለት “በስልጣን ሰንሰለታዊ ግንኙነት በፌደራል መንግስቱ ስር በማስገባት ማንኛውንም ትዕዛዝ እንዲቀበል የሚያደርገው አደገኛ አደረጃጀት የሚያስይዘው ነው” ሲል አስታውቋል።

“በአሁኑ ወቅት ክልሉ ያጋጠመው ችግር በህወሓት ውስጥ ያለ ችግር ብቻ አድርጎ ለማቅረብ እየተደረገ ያለው ጥረት ተቀባይነት የለውም” ያሉት ደብረጺዮን (ዶ/ር) “ኢህአዴግን ከውስጥ እንዳፈረሱት ሁሉ እነዚህ ሀይሎችም በህወሓት ውስጥ ሆነው ፓርቲውን ለማፍረስ ቢጥሩም ስላልተሳካላቸው አሁን ደግሞ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ሽፋን እየተንቀሳቀሱ ነው” በማለት ወቅሰዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here