በ5 ክልሎች በርካታ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን በምርመራ ማረጋገጡን የኢትዮጲያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽ አስታወቀ

0
333

ሐሙስ መስከረም 16 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ኮሚሽኑ በማእከላዊ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በጋምቤላ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ባለፉት ሦስት ወራት ተፈፀሙ ያላቸውን ከሕግ ውጭ የሆኑ ግድያዎች፣ የሲቪል ሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመት እና ዘረፋ ዘርዝሮ አውጥቷል።

በዚህም በ5 ክልሎች በርካታ ጥሰቶች በታጠቁ ሃይሎች ስለመፈጸሙ ነው የኮሚሽኑ ሪፖርት የሚያሳየው፡፡

ለአብነትም በአማራ ክልል ዋና ከተማ ባህርዳር የተፈጸሙ የቦንብ ጥቃቶችንና በኦሮሚያ ክልል ስለተፈጸሙ የዘፈቀደ ግድያዎች ያነሳው የመብት ተቋሙ ሪፖርት “ሸኔን እና ፋኖን ትደግፋላችሁ” የተባሉ ሰዎች ከቀናት እስከ ወራት ለእሥር መዳረጋቸውን ብሎም አሁን ድረስ ታሥረው የሚገኙ ሰዎች መኖራቸውን አስታውቋል።

ኢሰመኮ በኢትዮጵያ እገታ አስከፊ ገጽታ ያለው ችግር መሆኑን፣ የሀገር ውስጥ መፈናቀል፣ የመዘዋወር ነጻነትና ትራንስፖርት ላይ የተጣሉ “ሕገወጥ” ያላቸው ገደቦች የዜጎችን ሁለንተና ፈተና ውስጥ መጣላቸውን በምርመራ ውጤቱ ለማሳየት ጥሯል::

ክልሎች በግጭት ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት “ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተኩስ አቁም በማድረግ ለግጭቱ ሰላማዊ መፍትሔ ለማፈላለግ በቁርጠኝነት እንዲሠሩ የጠየቀው ኢሰመኮ በማናቸውም የግጭት ሂደት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች እና የሰብአዊነት ሕጎች ጥሰትን ከመፈጸም እንዲቆጠቡ፤ በግጭቱ የሚፈጸሙ ጥሰቶችን በይፋ እንዲያወግዙ እና ተጠያቂነትን እንዲያረጋግጡ፤ እንዲሁም በሚቆጣጠሯቸው አካባቢዎች ሰብአዊ መብቶችን አክብረው እንዲንቀሳቀሱ” ጠይቋል

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here